የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
ከተማ ግብርና ከምግብ ፍጆታ አልፎ የከተማችንን ውበትና የአየር ንብረት ሚዛን ለመጠበቅ፣ እንዲሁም ለወጣቶችና ለሴቶች ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠር ያለው ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው። ያለንን ውስን የከተማ መሬት በቴክኖሎጂና በዘመናዊ አሰራር በመደገፍ በጓሮ አትክልት፣ በዶሮ እርባታ፣ በንብ ማሳደግና በወተት ላም ልማት ረገድ አበረታች ውጤቶችን እያስመዘገብን እንገኛለን።
ይሁን እንጂ የጀመርናቸውን ስራዎች ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግና በየደረጃው ያሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችንን ማሳደግ የግድ ይላል። ጽ/ቤታችን አርሶ አደሩንና የከተማ ግብርና ባለሙያዎችን በዘመናዊ የእውቀትና የግብዓት አቅርቦት ለመደገፍ ቁርጠኛ ነው። ስራዎቻችንን በዲጂታል የመረጃ አያያዝ በማገዝ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለማድረስ እንዲሁም አዳዲስ የግብርና ግኝቶችን በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሰራን እንገኛለን። ... ተጨማሪ ያንብቡ
አቶ እንግዳው ጓዴ , የልደታ ክ/ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ