image
image
image
image
image

በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በከተማ ግብርና ዘርፍ በምግብ ራስን ከመቻል አልፎ የገበያ ማረጋጋት ስራው ላይ በርካታ ለውጦችን እያስመዘገበ ይገኛል።

ግንቦት 1, 2018
በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በከተማ ግብርና ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት ራስን በምግብ ከመቻል ባለፈ የገበያ መረጋጋትን በመፍጠር ረገድ ተጨባጭ ውጤቶች እያስመዘገበ ይገኛሉ። ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከኢኒሼቲቭ ግቦች መካከል በክፍለ ከተማው በልዩ ትኩረት ሲተገበር የቆየው የከተማ ግብርና የሌማት ትሩፋት ስራ በወተት፣ በንብ ማነብ፣ በዶሮ እርባታ፣ በእንቁላል ምርት እና በጓሮ አትክልት ልማት ላይ ምርትን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ችሏል። በከተማ ግብርና በሌማት ትሩፋት ስራዎች የአካባቢውን ማህበረሰብ የፍጆታ ፍላጎት ከመሸፈን ባለፈ ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ የኑሮ ውድነት ጫናን ለማቃለል የጎላ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። በክፍለ ከተማው የከተማ ግብርና ዘርፍ ከምግብ ዋስትና ባለፈ ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ የራሱን አዎንታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ የሚገኝ ሲሆን በተለይም በኢኮኖሚ አማራጭነት የነዋሪዎችን ገቢ ለማሳደግ ዓይነተኛ ሚና እየተጫወተ ነው። በአሁኑ ወቅት በክፍለ ከተማው በሚገኙ የተለያዩ የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ውስጥ የሌማት ትሩፋት ተግባራት ተጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን የከተማ ግብርናው የከተማዋን የምግብ ሥርዓት ለመቀየርና የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ በትኩረት እየተሰራበት ይገኛል።

መልዕክትዎን ይላኩ