ዜና | Oduu | News
"በባለፉት የለውጥ አመታት ውስጥ በከተማ ግብርና ዘርፍ በርካታ ሰው ተኮር የሆኑ ስራዎች መስራት ተችሏል።" አቶ ባዩ ሽጉጤ

በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ4ኛ አመት 4ኛ ዙር የሌማት ትሩፋት "በምግብ ራስን የመቻልና የስራ እድል ለመፍጠር" በሚል የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ። በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ባዬ ሽጉጤ ሲሆኑ በክቡር ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ አስጀማሪነት በከተማ ደረጃ የተጀመረው የከተማ ግብርና ስራ በርካታ የህብረተሰብ ክፍልና ቤተሰብ በቀጥታ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። አቶ ባዬ አክለው በባለፉት አምስት አመታት መንግስት ሰው ተኮር የሆኑ በርካታ ስራዎችን በከተማ ግብርና ዘርፍ መስራቱን አንስተው በከተማ ውስጥ ግብርናን በማስጀመር አበረታች ውጤት መመዝገቡን ገልፀዋል። በከተማ ግብርና ከስራ እድል ፈጠራው ባሻገር ከተረጂነት ወደ ማምረት የተሸጋገሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ቁጥራቸው ቀላል የማይባል በመሆኑ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽነሩ አስገንዝበዋል። የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በበኩላቸው በባለፉት የለውጥ አመታት ውስጥ ከተሰጡ ዋና ትኩረቶች ውስጥ ከተማን ከማዘመን ጎን ለጎን የከተማ ግብርና ስራ በማስጀመር በምግብ ራስን የመቻል ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል። ይህ ንቅናቄ ዋነኛ አላማው የተጀመረውን የከተማ ግብርንና በቀጣይነት በማስፋፋት ወጣቶችና ሴቶች የስራ እድል ፈጠራ እና በገበያ ላይ የሚታየውን የግብርና ውጤቶች የዋጋ ንረትን የማረጋጋት ስራ ለማሳለጥ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አያይዘው ጠቅሰዋል። ወ/ሮ ልዕልቲ እንዳሉት ከዚህ ቀደም በቤተሰብ ቢዝነስ ተደራጅተው ለሚሰሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከተደረገው ድጋፍ ባሻገር በዛሬው እለትም ከ800 በላይ ለሚሆኑ ነዎሪዎቻችን በዶሮ እርባታ ስራ እንዲሰማሩ ድጋፍ መደረጉን ጠቁመዋል። የክ/ከተማው አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንግዳው ጓዴ በበኩላቸው ይህ የኬጂ እና ዶር ድጋፍ ወጣቶች ተደራጅተው ስራ የሚፈጥሩበትና የገበያ ዋጋ የማረጋጋት ከፍተኛ ሚና አለው ብለው ክፍለ ከተማው በበጀት፣በግብአት እና በስልጠና ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በቀጣይም ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በከተማ ግብርና ዘርፍ በምግብ ራስን ከመቻል አልፎ የገበያ ማረጋጋት ስራው ላይ በርካታ ለውጦችን እያስመዘገበ ይገኛል።

በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በከተማ ግብርና ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት ራስን በምግብ ከመቻል ባለፈ የገበያ መረጋጋትን በመፍጠር ረገድ ተጨባጭ ውጤቶች እያስመዘገበ ይገኛሉ። ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከኢኒሼቲቭ ግቦች መካከል በክፍለ ከተማው በልዩ ትኩረት ሲተገበር የቆየው የከተማ ግብርና የሌማት ትሩፋት ስራ በወተት፣ በንብ ማነብ፣ በዶሮ እርባታ፣ በእንቁላል ምርት እና በጓሮ አትክልት ልማት ላይ ምርትን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ችሏል። በከተማ ግብርና በሌማት ትሩፋት ስራዎች የአካባቢውን ማህበረሰብ የፍጆታ ፍላጎት ከመሸፈን ባለፈ ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ የኑሮ ውድነት ጫናን ለማቃለል የጎላ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። በክፍለ ከተማው የከተማ ግብርና ዘርፍ ከምግብ ዋስትና ባለፈ ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ የራሱን አዎንታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ የሚገኝ ሲሆን በተለይም በኢኮኖሚ አማራጭነት የነዋሪዎችን ገቢ ለማሳደግ ዓይነተኛ ሚና እየተጫወተ ነው። በአሁኑ ወቅት በክፍለ ከተማው በሚገኙ የተለያዩ የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ውስጥ የሌማት ትሩፋት ተግባራት ተጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን የከተማ ግብርናው የከተማዋን የምግብ ሥርዓት ለመቀየርና የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ በትኩረት እየተሰራበት ይገኛል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክ/ከተማ "በአንስተኛ ቦታ የከተማ ግብርና ስራን በማከናወን ውጤታማ መሆን እንደሚቻል በተግባር ማረጋገጥ ችለናል"

"በከተማ ግብርና የተሰማሩ ዜጎች የምግብ ፍጆታቸውን ከመሸፈን ባለፈ ምርታቸውን ለገበያ በማቅረብ የኑሮ ውድነትን የማርገብ ስራ እያከናወኑ ይገኛሉ። ክ/ከተማችንን በሁሉም ዘርፍ መለወጥ እንደሚቻል በርትተን ከሰራን ለውጥ ማምጣት እንደምንችል የከተማ ግብርና ስራችን ሁነኛ ማሳያ ነው ። በከተማ ግብርና ስራችን የእለት የቤተሰብ ፍጆታን ከመሸፈን ባለፈ ለገቢያ በማቅረብ የገበያ ውድነትን እያረጋጋ ነው" የህብረተሰባችንን የኑሮ ውድነት ጥያቄን ለመመለስ የጀመርነውን የከተማ ግብርና ስራ ማጠናከር አለብን። በከተማ ግብርና ስራችን ችግር ፈች ስራ እየሰራን ነው። በቀጣይም ህዝባችንን ይዘን ተግተን እየሰራን ሁለንተናዊ ለውጥ ማምጣት ከሁላችን የሚጠበቅ ነው ። ህዝባችን ባላቸው ውስን ክፍት ቦታ በከተማ ግብርና ስራዎች ተሳትፈው በምግብ እራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል። አስተዳደሩ የሌማት ቱርፋት ስራን በክፍለ ከተማው ካስጀመረ ጊዜ አንስቶ በዘርፉ በተሰማሩ ዜጎች ላይ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችም ተመዝግበዋል። ዜጎች ባላቸው ክፍት ቦታ የከተማ ግብርናን ሰርተው ለውጤት መብቃታቸው ደግሞ የከተማ ግብርና ሰፊ ቦታን ብቻ ይፈልጋል ብለው በአመለካከት የታሰሩ አንዳንድ ዜጎችን አስተሳሰብ በእጅጉ ቀይሯል። እኛም እንላለን ባለን ውስን ቦታ ያለንን አቅም አሟጠን ከሰራን ለስኬት እንበቃለን፥ በምግብም የእለት ፍጆታችንን እንሸፍናለን። ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የ ልደታ ክ/ከተማ ኮሚንኬሽን ገፆችን ይከታተሉ !!

image
image
image
image