`

የዜጎች የስምምነት ሰነድ |
Citizens Charter

የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት እንደ ጽ/ቤት ከመቋቋሙ በፊት በንግድና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት ስር አንደ አንድ ቡድን የሚንቀሳቀስ ቢሆንም ብዙም አጥጋቢ ውጤት አላስመዘገበም ነግር ግን መንግስት ጥቅል ለአርሶ አደርና ለከተማ ግብርና ትኩረት በመስጠቱ ተጠቃሚዎች ከቤተሰብ ፍጆታ ማምርት አልፎ ተርፎም ለገብያ ማዋል እንደሚቻል ክብር ጠቅላይ ሚንስቴራችን ዶ/ር አብይ አህመድ ከገለጹ ቦኃላ ከተማ አስተዳደሩ ትኩረት በመስጠቱ በከተማ ደረጃ ፤ በኮሚሽን እንደ ክ/ከተማ እና ወረዳ ጽ/ቤት ሆኖ አንደ አዲስ ተቋቋሙዓል በዚህም በከተማ ግብርና በጣም አብዮት በሚባል ደረጃ የአመለካከት እና የተግባር ለውጥ ማምጣት ተችሎል በከተማችን ብሎም በክ/ከተማችን አንድም ክፍት ቦታ ሳይታረስ እንዳይቀር ብለን የጀመርነው ስራ በሌማት ቱሩፋት መርህ ግብር አስደማሚ ስራዎችን እየተሰሩ ይገኛል በአሁኑ ሰዓት በዚህ በያዝነው 2018 በጀት ዓመት በጓሮ አትክልትና በእንስሳት እርባታ ዘርፍ በቤተሰብ ፍጆታ ፤ በስራ ዕድል አዲስ ተጠቃሚዎች ወደ ስራ የገቡ ሲሆን፡፡ በእንስሳት እርባታ ዘርፍ ማለትም በወተት ከብት እርባታ ፤ በንብ ማነብ ፤ በዶሮ እርባታ 22332 ነባር ተጠቃሚዎችን እንዲሁም በእጽዋት ልማት ዘርፍ 43240 ተጠቃሚዎችን በአጠቃላይ 65572 ነባር ተጠቃሚዎችን በከተማ ግብርና በንቃት በክፍለ ከተማችን እየተሳተፉ ሲሆን ከዚህም በፊት በክፍትነት የምናውቃቸው የመንግስት እና የግል ተቋማት ሰፋፊ የእርሻ ስራ በተቀናጀ መልኩ እየተሰራና ለገብያ እየወጣ ይገኛል ይህ ለአዲስ አበባ ትልቅ እምርታ ነው፡፡
ማህረሰባችን ቀደም ሲል ያለው ግንዛቤ ከተማ ግብርና ሲባል የምናሾፍ ለራሳችን መቀመጫ የሌን እንዴት የጓሮ አትክልት ትከሉ ዶሮ አርቡ ትሉናላችሁ በሚል በጣም ይቃወሙ ነበር ነገር ግን በተደጋጋሚ ቤት ለቤተ በተሰራ የግንዛቤ ማስጨበጥ እና የመድረክ ስልጠና በአሁኑ ወቅት የነበረው አመለካከት ተቀይሮ ክፍት የሆነ ቦታ እየጠቆሙ ጭምር ቢሰራበት የሚል ጥያቄ እያቀረበ ይገኛል ትልቅ የሀሳብ ለውጥ ተፈጥሯዓል ከሁሉም በላይ የይቻላል መንፈስ መፍጠር ተችሎል ፡፡
በአሁኑ ሰዓት እንደ ልደታ ክፍከ ከተማ በሁሉም ወረዳዎቻችን በጓሮ አትክልትና በእንስሳት ዘርፍ በወተት ላም እርባታ እና በእንቁላል ጣይ ዶሮ ሞዴል የሆነ ብዙ ናቸው ከራሳቸው አልፈው ለገብያ እያቀረቡ ነው፡፡ በተቋማት ደረጃ የመንግስት መስተዳደር ተቋማት፤ በትምህርት ቤቶች ፤ጤና ጣቢያዎች እንዲሁም በስራችን የሚገኙ የተለያዩ የግል ድርጅቶች ሞዴል የሚሆኑ ስራዎች በአሳ ማርባታ ፤በእንቁላል ጣይ ዶሮ፤ በመሬትና በሽቅብ የጓሮ አትክልት ትልቅ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
የከተማ ግብርና ስራችን ውጤታማ እንዲሆን እና እንዲቀጥል በየወረዳው ከቤተሰብ ፍጆታ ያለፈ ምርት የሚያመርቱ አካላትን የገብያ ችግር እንዳይገጥማቸው በወረዳው የሰንደይ ማርኬት (የእሁድ ገብያ )እንዲሳተፍ እየተደረገ ይገኛል በተጨማሪም እንቁላል በቅናሽ ዋጋ እንደ ክፍለ ከተማ ለማዕከል ጋር በመነጋገር እየቀረበ ይገኛል፡፡
በከፍለ ከተማው ተሰማርተው ለሚገኙ ግለሰቦችና እና ማህበራት የድጋፍና ክትትል አግባባችንምን በተመለከተ የክትትልና ድጋፍ ኮሚቴ በማዋቀር ወደ ስራ የተገባ ሲሆን ለአስሩም ወረዳዎች ባለሙያዎችን በመደብ በሳምንት ሁለት ግዜ ክትትልና ድጋፍ በማድረጋ በየ ወሩ በክትትን ድጋፍ የተገኙ ውጤቶችን በመገምገም እስካሁን እየተሰራ ይገኛል፡፡
የአርሶ አደርና የከተማ ግብርና ስራችን በተጨባጭ ገብያ በማረጋጋት ውስጥ ጉልህ ሚና አለው በአሁኑ ሰዓት የከተማ ግብርና ውጤቶችን በክፍለ ከተማችን ብሎም እንደ ከተማ ገብያውን የማረጋጋት ስራ ከህብረት ስራ ጽ/ቤት ጋር በቅንጅት በመስራት የእንስሳት መኖዎችን (የእንቁላል ጣይ ዶሮ፤ የስጋ ዶሮ መኖ ፤የቄብ ዶሮ መኖ ፤የወተት ላም መኖ፤ የጊደር መኖ፤የጥጃ መኖዎችን) በቅናሽ ዋጋ ማቅረብ ተችሏ፡፡ በክ/ከተማችን ያሉ የከተማ ግብርና ተጠቃሚዎች ከቤተሰብ ፍጆታ አለፈው ገብያውን የማረጋጋት ስራ በደንብ እየተወጡ ይገኛል ይህ ተግባር እንዲቀጥል የሁላችንም ርብርብ ክትትል መጠናከር አለበት፡፡
በመጨረሻም የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ስራ ውጤቱ በተጨባጭ የሚታይ በሰዎች ኢኮኖሚ ላይ በቀጥታ ተፅኖ የሚያደርግ ነው ፡፡ ልደታ እንደ ሌሎች ማስፋፋያ ክፍለ ከተማ ሰፋፊ መሬት ባይኖርም ባሉ ክፍት ቦታዎች ላይ የተሰሩት ስራችዎች በቅንጅት በባለሙያ እና ከላይ እስከታች ያለው አመራራ ስለሚመራው ነው ፡፡ በመሆኑም አሁንም በተለያየ ጊዜ የሚገጥሙ ችግሮችን በርብርብ በመፍታት ውጤታማነቱን ማስቀጠል ያስፈልጋል ፡፡ በሌላ በኩል የክ/ከተማችን ወጣቶች በዚህ ዘርፍ ቢሰማሩ በአጭር ጊዜ ሀብት መፍጠር ሰለሚችሉ ተደራጅተው እንዲሰሩ ጥሪ እቀርባለው፡፡

የዜጎች ስምምነት ሰነድ ዓላማ

  1. ይህ የስምምነት ሰነድ ቢሮው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ዜጎች ህግና አሰራሩን ጠብቀው ያለምንም መሸራረፍ መብታቸውን በተሟላ መልኩ እንዲያገኙ ሲሆን ይህንንም ለአመራሩ፣ ለሰራተኛውም እና ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ግልጽ ለማድረግ ከዚህም ባሻገር ደግሞ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በማይወጡ አካላት ላይም ተቋሙ የገባውን የህሊና ውል መሰረት አድርጎ የተጠያቂነት አሰራርን ለማጎልበት ያለመ ነው፡፡

    የዜጐች የስምምነት ሰነድ አስፈላጊነት

    1. ተገልጋዮች ቢሮው በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ተጠቃሚ ሆነው እርካታቸውን የሚያሻሽል አገልግሎት ለመስጠት፤
    2. ህብረተሰቡን በማሳተፍ ፍትህዊ አገልግሎት ለመስጠት፤ ተገልጋዮች በቢሮው አገልግሎት አሠጣጥ ላይ የባለቤትነት ስሜት ተሰምቷቸው አስተያየት፤ ጥቆማና ግብዓት የሚሰጡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት፤
    3. ዜጎች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ (standard) ማግኘት እንደሚገባቸው ለማሳወቅ፤
    4. የዜጎችን የመረጃ ማግኘት መብት ለማረጋገጥ እና ቢሮው ለዜጎች ግልፅ፤ ቀልጣፋና ተጠያቂነት ያለበት አገልግሎት ለመሥጠት ያለመ መሆኑን ለማረጋገጥ፤

    የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት

      የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት በዝርዝር ለማወቅ ከፈለጉ ይህን Duties and Responsibility ይጫኑ

    ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች

    1. የከተማ ግብርና ልማት ማሳደግ
    2. ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ
    3. የግብርና ግብዓትና ምርት ጥራት ፤ ኃይጅንና ደህንነትን ማረጋገጥ
    4. የሴቶችና ወጣቶች ፍትሐዊ ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ማረጋገጥ
    5. የአርሶ አደር የልማት ተጠቃሚነትን ማሳደግ

    የስትራቴጂካዊ ውጤት

    1. ያደገ የከተማ ግብርና ልማት
    2. ያደገ የግብርና ምርት
    3. ጥራቱ ፤ ኃይጅንና ደህንነቱ የተረጋገጠ የግብርና ምርት
    4. የሴቶችና ወጣቶች ፍትኊ ተጠቃሚነት
    5. የለማ በዘላቂነት የተጠቀመ አርሶ አደር

    የደንበኞች መብቶች

    1. የመመካከር መብት፤፣
    2. ስለ አገልግሎቶቹ ሙሉ መረጃ የማግኘት፤ የመጠቀምና የሚጠይቀውን ወጭ የማወቅ፣፣
    3. ተገቢውን አገልግሎት ሳያገኝ ሲቀር ማስተካከያ የመጠየቅ፣
    4. ሁሉም አገልግሎቱን በእኩልነትና በፍትሐዊነት የማግኘትና የመጠቀም መብት፣ አላቸው።
    5. በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ ጥያቄ የመጠየቅ እና ማብራሪያ የማግኘት
    6. ተገልጋዮች አገልግሎቱን በሙሉ ወይም በከፊል ለማግኘት ሲመጡ ማሟላት ያለባቸውን ሁኔታዎች በቅድሚያ የማወቅ መብት አላቻው፡፡
    7. በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ አስተያየት /ቅሬታ የማቅረብ እና ላቀረቡት ጥያቄ ፍታሃዊ እንዲሁም ወቅታዊና በቂ መልስ የማግኘት፡፡
    8. ልዩ ትኩረት ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያየ መልኩ የመስተናገድና አገልግሎት የማግኘት፡፡
    9. በቢሮው ዕቅድ እና ግብረ-መልስ ላይ መሳተፍና አስተዋጽዖ የማድረግ፡፡

    የደንበኞች ግዴታዎች

    1. ሕጎችን እና የአሰራር መመሪያዎችን መከተል፤ ፣
    2. ትክክለኛ መረጃዎችንና ማስረጃዎች የማቅረብ ፣
    3. የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታን መከተልና ማሟላት፤
    4. አገልግሎት ሰጪ ተቋሙ ተገልጋዩን በጋራ በሚከናወኑ ተግባራት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ በጠየቀው ጊዜ ድርሻውን የመወጣት ግዴታ አለበት፡፡
    5. የአገልግሎት ክፍያ የመክፍል፤

    የተቋሙ ግዴታ

    1. አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ግብአቶች አሟልቶ መገኘት፣
    2. በተቀመጠው የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ መሰረት በክብር የማስተናገድ፤
    3. ለተገልጋዮች ፍትሃዊ፤ አድሎ የሌለበት አገልግሎት የመስጠትና በእኩልነት የማገልገል፣
    4. ቅሬታና አስተያየት ለመቀበልና ለመፍታት የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት የመዘርጋት፤
    5. ለሚቀርቡ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ፍትሀዊና ፈጣን ምላሽ የመስጠት፤
    6. ለተገልዮች የተቋሙን ዕቅድና የአፈፃፀም ሪፖርት ግልፅ ማድረግ አለበት፤
    7. በዜጎች የስምምነት ሰነድ መሰረት ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አስፈላጊ ግብዓቶችን የማሟላትና ተቋማዊ አቅም የመገንባት ግዴታ አለበት፡፡