image
image
image
image
image

"በባለፉት የለውጥ አመታት ውስጥ በከተማ ግብርና ዘርፍ በርካታ ሰው ተኮር የሆኑ ስራዎች መስራት ተችሏል።" አቶ ባዩ ሽጉጤ

ሚያዚያ 21, 2018
በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ4ኛ አመት 4ኛ ዙር የሌማት ትሩፋት "በምግብ ራስን የመቻልና የስራ እድል ለመፍጠር" በሚል የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ። በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ባዬ ሽጉጤ ሲሆኑ በክቡር ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ አስጀማሪነት በከተማ ደረጃ የተጀመረው የከተማ ግብርና ስራ በርካታ የህብረተሰብ ክፍልና ቤተሰብ በቀጥታ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። አቶ ባዬ አክለው በባለፉት አምስት አመታት መንግስት ሰው ተኮር የሆኑ በርካታ ስራዎችን በከተማ ግብርና ዘርፍ መስራቱን አንስተው በከተማ ውስጥ ግብርናን በማስጀመር አበረታች ውጤት መመዝገቡን ገልፀዋል። በከተማ ግብርና ከስራ እድል ፈጠራው ባሻገር ከተረጂነት ወደ ማምረት የተሸጋገሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ቁጥራቸው ቀላል የማይባል በመሆኑ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽነሩ አስገንዝበዋል። የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በበኩላቸው በባለፉት የለውጥ አመታት ውስጥ ከተሰጡ ዋና ትኩረቶች ውስጥ ከተማን ከማዘመን ጎን ለጎን የከተማ ግብርና ስራ በማስጀመር በምግብ ራስን የመቻል ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል። ይህ ንቅናቄ ዋነኛ አላማው የተጀመረውን የከተማ ግብርንና በቀጣይነት በማስፋፋት ወጣቶችና ሴቶች የስራ እድል ፈጠራ እና በገበያ ላይ የሚታየውን የግብርና ውጤቶች የዋጋ ንረትን የማረጋጋት ስራ ለማሳለጥ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አያይዘው ጠቅሰዋል። ወ/ሮ ልዕልቲ እንዳሉት ከዚህ ቀደም በቤተሰብ ቢዝነስ ተደራጅተው ለሚሰሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከተደረገው ድጋፍ ባሻገር በዛሬው እለትም ከ800 በላይ ለሚሆኑ ነዎሪዎቻችን በዶሮ እርባታ ስራ እንዲሰማሩ ድጋፍ መደረጉን ጠቁመዋል። የክ/ከተማው አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንግዳው ጓዴ በበኩላቸው ይህ የኬጂ እና ዶር ድጋፍ ወጣቶች ተደራጅተው ስራ የሚፈጥሩበትና የገበያ ዋጋ የማረጋጋት ከፍተኛ ሚና አለው ብለው ክፍለ ከተማው በበጀት፣በግብአት እና በስልጠና ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በቀጣይም ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ