የልደታ ክ/ከተማ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ሥልጣንና ተግባራት ተሰጥተውታል
- የከተማ የግብርና ምርት በጥራት የሚመረትበትን ፤ ለገቢያ የሚቀርብበትን እና የግብርና ልማት የሚጎለብትነትን ስልት ይቀይሳል ፤ ያስፈጽማል፡፡
- ነዋሪዎች በከተማ ግብርና እንዲሳተፉ ያበረታታል ፤ በተለያዩ የግብርና ዘርፍ ለተሰማሩ አካላት ምርትና ምርታማነታቸውን እንዲጨምር ዘመናዊ የግብርና ግብዓት እንዲቀርብላቸው ሙያዊ ድጋፍና ምክር እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
- የእንስሳት በሽታዎች ስርጭትን ያጠናል፤ በበሽታ ስርጭት የተነሳ መውሰድ ያለባቸውን እርምጃዎች ለመንግስትና ለአርቢዎች ያሳውቃል፤ ለእንስሳት አርቢዎች የእንስሳት ህክምናና የክትባት አገልግሎት ይሰጣል፤እንዲሰጥ ያደርጋል፤የዕብድ ውሻ በሽታ መከላኪያ ክትባት ይሰጣል፡ታክመው መዳን የማይችሉ እና የሌላቸውን እንስሳት ያስወግዳል፡፡
- ለእንስሳት አርቢዎች የማዳቀል አገልግሎት ይሰጣል፤ የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂ ውጤቶች፤ ምርጥ ዘርና ማደበሪያ ለአርሶ አደር እንዲደርስ ያደርጋል፤ ውጤታማነታውንም ይከታታላል፤ ለአርሶ አደሮች ትምህርትና ስልጠና እንዲሁም የሙያ ድጋፍ ይሰጣል፡፡
- የእንስሳትና የእጽዋት የኳራንቲን አገልግሎት ይሰጣል ፤ በከተማው ውስጥ አገልግሎት ላይ ሊውል የሚችል የእንስሳት መድሃኒቶች ጥራት ደረጃቸውን የጠበቁና የአገልግሎት ዘመናቸው ያላለቀ መሆኑን ያረጋግጣል ፤ የአገልግሎት ዘመናቸው ያለፈ መድሃኒቶች ለሚያስወግድ አካል ያሳውቃል፡፡
- በህግ በሌላ ሁኔታ የተደነገገው እንደተጠበቀው ሆኖ በመንግስት ፤ በማህበራት እና በግል ቄራ ድርጅት የእርድ እንስሳትና ስጋ ምርመራ አገልግሎት ይሰጣል ፤ ይቆጣጠራል ፤ ህገ ወጥ የእንስሳት እርድና በህገ ወጥ መንገድ የታረዱ ስጋ ዝውውርን ይቆጣጠራል ፤ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወስዱ ያደርጋል፡፡
- አርሶ አደሮች ባላቸው ይዞታ ላይ በግላቸው ፤ ከአርሶ አደር ጋር በመደራጀት ወይም ከባለሀብት ጋር በመጣመር እንዲያለሙ አሰራር ይዘረጋል፡፡
- ለልማት ይዞታቸውን የለቀቁ የልማት ተነሺዎችን መረጃ አደራጅቶ ይይዛል ፤ አግባብ ባለው ህግ መሰረት ተቢውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡
- ለልማት ይዞታቸውን የለቀቁ ተነሺ አርሶ አደሮች የተሰጣቸውን ካሳ አቀናጅተው ወደ ተሻለ ልማትና የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ በግል ይዞታቸው ወይም ተደራጅተው የሚሰማሩበትን ስልት ይቀይሳል ፤ ተግባራዊ ያደርጋል ፤ይደግፋል ፤ ይከታተላል፡፡