image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ የዶሮ ኬጅና የእንቁላል ጣይ ዶሮ ድጋፍ ተደረገ።

ህዳር 7, 2018
በልደታ ክፍለ ከተማ የነዋሪዎችን የኢኮኖሚ አቅም ለማጠናከር፣ የሥራ ዕድልን ለማስፋፋትና የቤተሰብ ገቢን ለማሳደግ ያለመ የዶሮ ኬጅና የእንቁላል ጣይ ዶሮ ከከተማ በተረገ ድጋፍ ለወረዳዎች ተሰጠ። የክ/ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አዳሙ በዛብህ እንደተናገሩት ድጋፉ ነዋሪዎች በዶሮ እርባታ ሥራ በመሰማራት የራሳቸውን የገቢ ምንጭ እንዲፈጥሩ፣ ከእንቁላል ምርት ገቢ እንዲያገኙና በአካባቢው የምግብ አቅርቦት ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡ የሚያስችል መሆኑ ገልፀዋል። የዶሮ ኬጅና የእንቁላል ጣይ ዶሮ ድጋፉ ተጠቃሚዎች የዶሮ እርባታን እንደ ዘላቂ የኑሮ መሻሻያ አማራጭ እንዲጠቀሙበት የተጀመረውን ሥራ ወደ ተሻለ የምርት ደረጃ እንዲያሳድጉ የሚያግዝ ነው ብለዋል። የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበበ ዱላ እንደተናገሩት ድጋፉ የስራ ዕድልን ከመፍጠር ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ያስችላል ብለዋል። ተጠቃሚዎች በበኩላቸው ድጋፉ የቤተሰብ ገቢን ከማሳደግ ባለፈ የአካባቢውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማሳደግ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ